የጽ/ቤቱ ኃላፊ መልእክት
የልደታ ክፍለ ከተማ ንግድ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት የተቋሙን የልማት እቅድ ነባራዊ መነሻን መሰረት በማድረግና መልካም አጋጣሚዎችን ታሳቢ በማድረግ ያቀደ ሲሆን ይህን እቅድ ለተቋሙ አመራሮች፤ ፈፃሚዎች፤ ባለድርሻ አካላትና የህዝብ ክንፍ በየደረጃው የጠራ ውይይት እንዲያደርጉበት ተደረገ ሲሆን በውይይቱ የተገኙ ግብዓቶችን መሰረት በማድረግ አስፈላጊዉ የማሻሻያ እርምጃ ተወስዷል፡፡ በዚህ መሰረት በተግባር ምዕራፍ በህግ ማስከበር፤ ነጋዴ ቁጥር ማሳደግ፤የምርት አቅርቦትና የሸማቾች መብት በማስጠበቅ በተሰሩ ስራዎች በአመቱ ውጤታማ እንዲሆን አስችሎታል፡፡
በበጀት ዓመቱ በተቋሙ አሰራርና መመሪያ ዙሪያ፤ ከህገወጥ ንግድ ነፃ የሆነ ቀጠና፤የምርት አቅርቦት በእሁድ ገበያ፤ በሸማችና በነጋዴዎች፤ የገቢ አቅምን ማሳደግና በመሳሰሉት ተግባራት በተሰራው ስራ ሰፋ ያለ የህብረተሰብ ክፍል ግንዛቤ እንዲፈጠርለት ተደርጓል፡፡
የእሁድ ገበያ በነጋዴ አመራረጥ፤ በቦታ መረጣ፤ በምርት አቅርቦትና በዋጋ ተወዳዳሪነት የተሻሉ እንዲሆኑ ተደጋጋሚ መድረኮች ከአመራሩና ከነጋዴዎች ጋር የተፈጠረ ሲሆን በቂ የሰራተኛ ስምሪት በማድረግ ቁጥጥር የተደረገ ሲሆን መሰረታዊ የሆነ ጥፋት ውስጥ ገብተው የተገኙ ተሳታፊዎች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ ተወስዷል፡፡
ወ/ሮ ተስፋነሽ ጋሻዉ
, የልደታ ንግድ ጽ/ቤት ኃላፊ
በበጀት ዓመቱ በተቋሙ አሰራርና መመሪያ ዙሪያ፤ ከህገወጥ ንግድ ነፃ የሆነ ቀጠና፤የምርት አቅርቦት በእሁድ ገበያ፤ በሸማችና በነጋዴዎች፤ የገቢ አቅምን ማሳደግና በመሳሰሉት ተግባራት በተሰራው ስራ ሰፋ ያለ የህብረተሰብ ክፍል ግንዛቤ እንዲፈጠርለት ተደርጓል፡፡ የእሁድ ገበያ በነጋዴ አመራረጥ፤ በቦታ መረጣ፤ በምርት አቅርቦትና በዋጋ ተወዳዳሪነት የተሻሉ እንዲሆኑ ተደጋጋሚ መድረኮች ከአመራሩና ከነጋዴዎች ጋር የተፈጠረ ሲሆን በቂ የሰራተኛ ስምሪት በማድረግ ቁጥጥር የተደረገ ሲሆን መሰረታዊ የሆነ ጥፋት ውስጥ ገብተው የተገኙ ተሳታፊዎች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ ተወስዷል፡፡
ወ/ሮ ተስፋነሽ ጋሻዉ , የልደታ ንግድ ጽ/ቤት ኃላፊ