image
image
image
image
image

የልደታ ክፍለ ከተማ ንግድ ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወር አፈፃፀም እውቅናና ሽልማት አካሄደ።

የካቲት 4, 2018
በመድረኩም የ2018 በጀት አመት የቀሪ 6 ወራት የተከለሰ እቅድ የጋራ ተደርጓል። በእውቅናና ሽልማቱ የወረዳ አመራሮች ፣ የምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴዎች እንዲሁም የዘርፉ ሰራተኞችና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወር አፈፃፀም እውቅናና ሽልማት ተሰጥቷል። የልደታ ክፍለ ከተማ ንግድ ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ተስፋነሽ ጋሻው በእውቅናና ፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው እንደተናገሩት ባሳለፍነው 6 ወር የተሻለ የንግድ ስርዓት እንዲኖር ወጥ የሆነ እቅድ ታቅዶ ውጤታማ ስራዎች መሰራታቸውን ገልፀው እቅዱ ተግባራዊ እንዲሆን ውጤታማ የሆነ ድጋፍና ክትትል መደረጉን ተናግረዋል:: የንግድ ስርዓቱን በማዘመንና በቴክኖሎጂ እንዲታገዝ በማድረግ ቀልጣፋና ተደራሽ አገልግሎት መስጠት ያስፈልጋል ያሉት ወ/ሮ ተስፋነሽ ጋሻው አያይዘው ገበያውን ለማረጋጋት የተቋቋሙት የእሁድ ገበያ መዳረሻ ቦታዎች በቂ የምርት አቅርቦት እንዲኖርና በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲሸጥ አስፈላጊውን ድጋፍና ተገቢውን ቁጥጥር በማድረግ ባሳለፍነው 6 ወር የተሻለና ውጤታማ ስራዎች መሰራቱን ተናግረዋል:: የልደታ ክፍለ ከተማ ንግድ ፅ/ቤት በ2018 በጀት አመት የ6 ወር የዕቅድ አፈፃፀም ምዘና በማድረግ የላቀ አፈፃፀም ለነበራቸው ተቋማትና ባለሙያዎች ዕውቅናና ማበረታቻ ሽልማት በሰጠበት በበጀት አመቱ በ6 ወሩ ውስጥ ደረጃ ውስጥ ለገቡ ወረዳዎች የዋንጫ እና የሰርተፍኬት ሽልማት ተሰጥቷቸዋል። በዚህም መሰረት :- ወረዳ 8 ንግድ ጽ/ቤት 1ኛ ወረዳ 4 ንግድ ጽ/ቤት 2ኛ ወረዳ 1 እና 10 ንግድ ጽ/ቤት 3ኛ በመሆን የዋንጫ ተሸላሚ ሆነዋል። በቅዳሜና እና እሁድ ገበያ ስታንዳርድ በማስጠበቅ ወረዳ 7 የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል።

መልዕክትዎን ይላኩ