image
image
image
image
image

የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር ንግድ ጽ/ቤት የ2017 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀሙን ከባለድርሻ አካላት ጋር ገመገመ።

ሀምሌ 8, 2018
የጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ተስፋነሽ ጋሻው በግምገማው ወቅት እንደተናገሩት ባለፈ ዓመት ተቋሙ በርካታ ተግባራት እንዳከናወነ ገልፀው በዚህም በክ/ከተማ በሚገኙ 10 የእሁድ ገበያ ላይ የሰብል፣ ኢንዱስትሪ፣ አትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም የእንስሳት ተዋጾ ምርት አቅርቦት መሠረት በማድረግ ውጤታማ ስራ እንደተሰራ ገልፀዋል። ኃላፊዋ አክለውም በህብረት ሥራና ሸማች ማህበራት የተለያዩ የፍጆታ ዕቃዎችንና ምርቶች የመሰብሰብ፣ የመከዘንና የማከመቻት ስራ ፥በንግድ ስራ ድርጅት አማካይነት የድጎማ ምርት በማቅረብ ለማህበረሰብ ስርጭት ማካሄድ ባለፈ ዓመት በውጤታማነት የተሰሩ ስራዎች መሆናቸውን ተናግረዋል። ከከተማ ጀምሮ እስከ ወረዳ የህገ -ወጥ ቁጥጥር ግብረ ሀይል ተዋቅሮ የቁጥጥር ስራ እየተሰራ መሆኑን የገለፁት ኃላፊዋ በዚህም ያለንግድ ፈቃድ፣ ባልታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ ከአድራሻ ውጪ የሚሰሩ፣ ከተሰጣቸው ዘርፍ ውጪ የሚሰሩ፣ የጥራት ችግር ያለባቸውን ምርቶች የሚያቀርቡ፣ ያለደረሰኝ ግብይት የሚፈጽሙ፣ እሴት ታክስ ያልተመዘገቡ፣ ምርት የሚያከመቹ መጋዘን የመፈተሽ ስራ ተሰርቷል እርምጃ የመውሰድ መከናወኑን ተናግረዋል። ወ/ሮ ተስፋነሽ አክለውም በ 2017 ዓ.ም አፈፃፀማችን እቅድን መሠረት አድርጎ ከመፈፀም አንፃር ተቋሙ ያለበት ሁኔታን በርካታ ተግባራት እንዳከናወነ በመግለፅ በክፍተት የታዩትን በቀጣይ በማስተካከል አሁን ካለን አገልግሎት አሰጣጥ የተሻለ እንዲሆን በቅንጅት በትስስር መስራት አለብን በማለት ገልፀዋል። በተደረገው የድጋፍና ክትትል ላይ የጋራ መግባባት ፈጥሮ ውጤት በማምጣት የተሻለ አገልግሎት መስጠት የሚችል ተቋም መገንባት ችለናል በማለት ገልፀዋል ኃላፊዋ። የመድረኩ ተሳታፊዎች በዚህ ልክ ውይይት መደረጉ የተሻለ ሲሆን በቀጣይ የሚከናወኑ ተግባራቶች የሚሰጠው አገልግሎት ቀልጣፋ እንዲሆን በጋራ መስራት ይኖርብናል በማለት ገልፀዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች