image
image
image
image
image

መስቀል በዓል ምክንያት በማድረግ የተለያዩ ምርቶች የሚቀርቡበት ደማቅ የበዓል ባዛር መከፈት መቻሉ ተገለፀ።

መስከረም 15, 2018
"በእምርታ እና በማንሰራራት የታጀበ ህዝባዊ በዓላት በጋራ እናክብር" በሚል መሪ ቃል የመስቀል በዓልን ምክንያት በማድረግ ባዛር ተከፍቷል። ባዛሩን የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ንግድ ጽ/ቤት፣ ህብረት ስራ ጽ/ቤት ፣ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት ፣አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ጽ/ቤት በቅንጅት አዘጋጅተዋል በባዛር ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የልደታ ክ/ከተማ ምክትል ስራ አስፈፃሚና ስራና ክህሎት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አራርሳ ድሪባ እንደተናገሩት ባዛሩ በርካታ የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርቶች በስፋትና በጥራት የቀረቡበት መሆኑንና ባዛሩ የበዓል ገበያን በማረጋጋት ረገድ ከፍተኛ ሚና እንዳለዉ በመግለፅ የክ/ከተማው ማህበረሰብ በባዛሩ በመገኘት የተለያዩ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲገበይ ጥሪ አቅርበዋል። የአዲስ አመት ባዛርን በጥሩ ሁኔታ ካጠናቀቅን በኋላ የመስቀልን በመጀመር ለማህበረሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ የተለያዩ ምርቶችን ማቅረብ መቻሉን የገለፁት አቶ አራርሳ አያይዘው ማህበረሰቡ በተዘጋጀው ባዛር የቀረበውን ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ መገብያየት እንደሚችሉም ገልፀዋል። የልደታ ክፍለ ከተማ ንግድ ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ተስፋነሽ ጋሻው በበኩላቸው ባዛሩ የመስቀል በዓልን ምክንያት በማድረግ የተከፈተ ሲሆን በባዛሩ የተለያዩ የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶችን በማካተት በቂ አቅርቦት መኖሩን ጠቅሰዉ በዓልን ተከትሎ ሊከሰት የሚችል የምርት አቅርቦት እጥረትና የዋጋ ንረት የሚከላከል መሆኑን ገልፀዋል ። በበዛሩ የተለያዩ ለበዓል ፍጆታ የሚውሉ ግብዓቶች ያካተተ ነው ያሉት ወ/ሮ ተስፋነሽ አያይዘው ማህበረሰብ የቀረበውን ምርት እስከ መስቀል ድረስ በባዛሩ ተገኝተው መገበያየት እንደሚችሉ ገልፀዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች