Welcome to Lideta Subcity Trade Office!       እንኳን ወደ ልደታ ክ/ከተማ የንግድ ጽ/ቤት በሰላም መጡ!       ጽ/ቤቱ ልደታ ክ/ከተማ ዘመናዊ፣ ፍትሃዊና ተወዳዳሪ የንግድ ማዕከል ከሆኑ የአዲስ አበባ ክፍለ ከተሞች ግንባር ቀደም እንድትሆን ይተጋል!!

የጽ/ቤቱ ኃላፊ መልእክት

የልደታ ክፍለ ከተማ ንግድ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት የተቋሙን የልማት እቅድ ነባራዊ መነሻን መሰረት በማድረግና መልካም አጋጣሚዎችን ታሳቢ በማድረግ ያቀደ ሲሆን ይህን እቅድ ለተቋሙ አመራሮች፤ ፈፃሚዎች፤ ባለድርሻ አካላትና የህዝብ ክንፍ በየደረጃው የጠራ ውይይት እንዲያደርጉበት ተደረገ ሲሆን በውይይቱ የተገኙ ግብዓቶችን መሰረት በማድረግ አስፈላጊዉ የማሻሻያ እርምጃ ተወስዷል፡፡ በዚህ መሰረት በተግባር ምዕራፍ በህግ ማስከበር፤ ነጋዴ ቁጥር ማሳደግ፤የምርት አቅርቦትና የሸማቾች መብት በማስጠበቅ በተሰሩ ስራዎች በአመቱ ውጤታማ እንዲሆን አስችሎታል፡፡

በበጀት ዓመቱ በተቋሙ አሰራርና መመሪያ ዙሪያ፤ ከህገወጥ ንግድ ነፃ የሆነ ቀጠና፤የምርት አቅርቦት በእሁድ ገበያ፤ በሸማችና በነጋዴዎች፤ የገቢ አቅምን ማሳደግና በመሳሰሉት ተግባራት በተሰራው ስራ ሰፋ ያለ የህብረተሰብ ክፍል ግንዛቤ እንዲፈጠርለት ተደርጓል፡፡ የእሁድ ገበያ በነጋዴ አመራረጥ፤ በቦታ መረጣ፤ በምርት አቅርቦትና በዋጋ ተወዳዳሪነት የተሻሉ እንዲሆኑ ተደጋጋሚ መድረኮች ከአመራሩና ከነጋዴዎች ጋር የተፈጠረ .... ተጨማሪ ያንብቡ

ወ/ሮ ተስፋነሽ ጋሻዉ , የልደታ ንግድ ጽ/ቤት ኃላፊ
image description

ዋና ዋና አገልግሎቶች

የዘርፍ ማህበራትና የነጋዴ ፎረሞችን በማደራጀት እዉቅና መስጠት
መሰረታዊ ሸቀጦች ትስስርና ስርጭት አገልግሎት
የገበያ ዋጋ መረጃ መስጠት
ንግድ ማህበራት የድርጅት ስም ማጣራት
የንግድ ነክ መረጃ በክፊያና ያለክፊያ መስጠት
የአክሲዮን ማህበራት ክትትልና ድጋፍ ማድረግ
የካፒታል እቃ ዉል ምዝገባና ስረዛ ማድረግ
ሸማቹ ማህበረሰብ የሚያቀርቧቸዉን አቤቱታዎችና ቅሬታዎች መቀበልና መፍታት

የጽ/ቤቱ ቡድን መሪዎች

ወ/ሮ የሺ ለማ

የሸማች መብት ጥበቃ ቡድን መሪ

ወ/ሮ አልማዝ ሰሶ

የኢንስፔክሽንና ሬጉላቶሪ ቡድን መሪ

አቶ አይቸዉ ንጋቱ

የበገያ መረጃ ቡድን መሪ

ወ/ሮ ሂሩት በቀለ

የንግድ ግብይት ማስፋፊያ ቡድን መሪ

ወ/ሮ ትዝታ ድሪባ

መደበኛ ያልሆነ ንግድ ስርአት ማስያዝ ቡድን መሪ

ወ/ሮ ጌጤነሽ ተካልኝ

የንግድ ምዝገባና ፈቃድ ደንበኞች አገልግሎት ቡድን መሪ

በልደታ ክ/ከተማ ንግድ ጽ/ቤት

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የልደታ ክ/ከተማ ንግድ ጽ/ቤት ከተሰጠው ተግባርና ኃላፊነት መነሻ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታትና የለውጥ ሥራዎችን ቀጣይነት ለማረጋገጥ የተቋሙን አገልግሎት አሰጣጥ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ በብቃቱና እና በሥነ-ምግባሩ የተመሰገነ የሰው ኃይል እንዲመራ በማድረግ ለተገልጋዮቹ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በአዲስ መልክ በመለየት አደራጅቷል፡፡

በተጨማሪም በጽ/ቤት የሚሰጠው አገልግሎት የተገልጋይ ፍላጎትን ማዕከል አድርጎ ይበልጥ ተደራሽ እንዲሆን ለማስቻል የሚሰጡ የአገልግሎት አይነቶች፣ አገልግሎቱ የሚሰጥበት ስታንዳርድ፣ የሚሰጥበትን ቦታ እና ከተገልጋይ የሚጠበቁ ቅድመ ሁኔታዎችን በግልጽ በዝርዝር በማስቀመጥ የጽ/ቤቱ ሠራተኞች በተቀመጠላቸው ስታንዳርድ መሰረት ፍህታዊና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲሰጡና ተገልጋዮች ምን ዓይነት አገልግሎት በምን ዓይነት ደረጃ ማግኘት እንደሚገባቸው ግንዛቤ በመፍጠር በዚህም ግልፅነትና ተጠያቂነት እንዲኖር፣ በህዝብና መንግስት መካከል መተማመን እንዲፈጠር፣ ልማትና ዲሞክራሲ እንዲያብብ ትልቅ አስተዋጽኦ አላቸው፡፡ በመሆኑም የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በዘላቂት ለመፍታት በምናደርገው ጥረት ባለድርሻ አካላትና ህብረተሱቡ ከጽ/ቤቱ ጎን እንዲቆሙ እናሳስባለን፡፡